የአውሮፓ ህብረት ሪፖርት የተቃዋሚዎችን አሸናፊነት አረጋግጧል

በህብረቱና በቅንጅቱ መሪዎች ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱት የመንግስትና የፓርቲው ሚዲያዎች ፊታቸውን ወደ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች አዙረዋል። በዚህም የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢ ልዑካን መሪዎች «ስውር ነጋዴዎች» በሚል ዘለፋ ወርዶባቸዋል። የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን ባቀረበው የናሙና ጥናት ኢሕአዴግ 36 በመቶ ድምፅ አግኝቶ ሲሸነፍ፣ ቅንጅቱ 47 በመቶ ከፍተኛ ድምጽ ማግኘቱን ህብረትና ሌሎች ፓርቲዎች ደግሞ 17 በመቶ ድምፅ ማግኘታቸው ተመልክቷል። ይህም በቅርቡ ይፋ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የናሙና ጥናት እንደሚያሳየው ቅንጅቱ ከህብረቱ ጋር በመሆን የፌዴራሉን መንግስት መረከብ የሚያስችለው ነው። ኢህአዴግ አጋሮቼ ከሚላቸው ፓርዎች ጋር ቢሆንም እንኳን መንግስት መመስረት የሚያስችል ድምፅ እንዳላገኘ ጥናቱ አመልክቷል። ይህን ጥናት ለማስለወጥ በኢሕአዴግ በኩል የተደረገው ሙከራ መክሸፉ በህብረቱ ታዛቢ መሪዎች ላይ የማጥላላት ዘመቻው ለመከፈቱ ምክንያት እንደሆነ ታምኖበታል።

መንግሥታዊው ኢትዮጵያን ሄራልድ ዕለታዊ የእግሊዝኛ ጋዜጣ ረቡዕ እ/ኤ/አ በኦገስት 17/2005 «ጉሜ እና ክላርክ ገለልተኛ ታዛቢዎች ወይንስ ስውር ነጋዴዎች?» በሚል ርዕስ ባቀረቡት ዘገባ ሁለቱን ከፍተኛ ልዑካን ቀጥቅጠዋቸዋል። ይህ ጽሁፍ በብዕር ስም የቀረበ የመንግስት ባለሥልጣናት አቋም እንደሆነም ታዛቢዎች ያጠራጠረ አልሆነም። በእነዚህ ከፍተኛ ልዑካን ላይ በመንግስት ሚዲያ ከትችቱ ባሻገር ወደ ዘለፋና ስም ማጥፋት የወረደ ዘመቻ መጀመሩ አነጋጋሪ ሆኗል።

«...በግንቦቱ 7/1997 ምርጫ የአና ጉሜዝና ቲም ክላርክ ድርጊቶች እንደ ቱሪስት እንጂ እውነተኛ ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፈን የሚረዳ አይመስለንም» የሚለው በሄራል ጋዜጣ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ ሲቀጥልም «ይህ ፀሀፊ ኢ-ሞራላዊ ናቸው ብሎ የተመለከታቸውን ወገናዊ እንቅስቃሴዎች ከዚህ በታች እንመልከት። ካለ በኋላ በግለሰቦቹ ላይ ከፍተኛ ዘለፋ አውርዷል።

ከአባይ ነሐሴ 14 ቀን 1997

ሰለ እዚህ ዜና ዋርካ ስር በአማርኛ ይወያዩ !